Saturday, January 2, 2016

የዲሞክራሲ መብቶችን በማፈን የሚድያ ነፃነት አይረጋገጥም!!



   አለማችን ለመገመቱ እጅግ በሚያስቸግር የግሎባላይዜሽን   መተሳሰር ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ  እንቅስቃሴ በመፍጠር አገሮች ከራሳቸው ሁኔታ ተነስተው ለውጥ ለማምጣትና  የተሻሻለ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ላይና ታች በሚሉበት ጊዜ፣ ህዝቦችም በየእለቱ ለሚከሰቱት የአገራቸውና አካባቢዎቻቸው ሁኔታን ግንዛቤ እንዲያሳድሩ የተሻለ ህይወትና ተስፋ የሚሹበት ጊዜ ሆኖ እናገኘዋለን።
     በሌላ በኩል ደግሞ የዜጎች  ዲሞክራሲያዊና ሰብኣዊ መብቶችን  የማፈን ተግባር  እንደ አንድ አላማ አድርገው በመውሰድ  ፖለቲካዊ ስልጣናቸውን ለማራዘም የሚያድረጉት ደባ፣ አሁን ባለንበት በሰለጠነ ዘመን ይፈፀማል ተብሎ  ለማመኑ በሚያስቸግር፤ መብታችን ይከበር  ብለው ለጠየቁና ተቃውሞቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ላካሄዱ ንፁሃን ዜጎች በጎደና እያለቁ መታዘብ እለታዊ ፍፃሜ ሁኗል።
    በዚህ መሰረትም ሃገራችን ኢትዮጵያ የዚህኛው አስራር ሰለባ በመሆንዋ፤ አግባብነት በጠፋቸውና አምባገነን በሆኑት የኢህአዴግ ባለ ስልጣኖች የዲሞክራሲ መብት በሚል ፈሊጥ በተለያዩ መድረኮችም ሆነ የግል ሚድያዎቻቸው ተጠቅመው ቅስቀሳ  ከጀመሩ  ሩብ ዘመን ያህል  አስቆጥረዋል።  
  ባለፉት በእያንዳንዳቸው የስርአቱ የአገዛዝ አመታት  ዲሞክራስያዊ  መብታችን ይከበር በማለት በስርአቱ ፕሮፖጋንዳ ተታልለው  በየጎደናው ሰልፍ  ለወጡት ንፁሃን ወገኖቻችን ላይ ሂይወታቸው መና ሁኖ ሲቀር፣ አብዛኛዎችም በስርአቱ ወጥመድና  ተንኮል  ባልዋሉበት  የሃሰት ወንጀል ሲያዙ ከታችኛው እስከ ላይኛው የወንጀለኞች ምርመራ ውስጥ ገብተው ያለ ርህራሄ እንዲሰቃዩ በማድረግ ለሌሎች አስጊ ናቸው የተባሉት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችም ለዘመናት  ተፈርደው በቁጥጥር ሰር ገብተው ይገኛሉ።
      እነዚህንና ሌሎችን የሚፈፀምባት አገር ህዝብ ስለ አገሩ  አጠቃላይ ሁኔታ መረጃ የማግኘት መብት አለው ከማለት የለውም ብሎ መግለፅ ይቻላል፣ ምክንያቱም ህዝብ በአገሩ የሚካሄዱት አጠቃላይ ፍፃሜዎች  ትክክለኛና ያልታዛባ መረጃ ሊያገኝ ሳይሆን የስርአቱ ፍላጎትና ትእዛዝ ብቻ  የሚፈፅሙና የሚተገብሩ ጋዜጦችና  ሚዲያዎች ብቻ እንዲሆን አድረገውታል፣
 በመሆኑም በስርአቱ ሚድያዎች  ተቀርቅረው የሚሰሩ ጋዜጠኞች እውነተኛ ትኩስ መረጃ ወደ ህዝብ እንዲዳረስ ከማድረግ ይልቅ በመሬት ላይ የሌለ የተዛባና የተጋነነ የልማት እንቅስቃሴዎችንና ዜማዎች የተድበሰበሰ መደቦችን በማስተላለፍ ላይ ተጠምድው ይገኛሉ።
   ሆኖም ግን በአገራችን የሚፈፀሙ ተጨባጭ ሁኔታዎች  ለህዝብ እንዳይደርሱ አግደው በመያዝ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ከውጭ የሚተላለፉ ነፃ ሚድያዎች እውነትኛ ምስሎችና ለሚፈፀሙት  እለታዊ ተግባሮቻቸው ተጋልጦ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ  ከህዝብ  በማጭበረበር በሚሰበሰብ ገንዘብና ከውጭ በእዳ በሚገኘው  በቢልዮኖች የሚገመት  ገንዘብ  ለመሰረተ ልማትና ለህዝቦች ጥቅም ሳይውል በቀጥታና በተዘወዋሪ መንገዶች ተጠቅመው ብዙ ገንዘብ በማፍሰስ በማፈን ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደቆዩና አሁንም እንዳሉ ሁሉም የአገራችን ዜጋ የሚያውቀው ሃቅ ነው።
    ይህም ደግሞ ውስጣዊ ተግባራቸውና ብልሹ አሰራራቸው  ቁልጭ አድርጎ  የሚያሳይና  በይበልጥ መጥፎ አሰራሩን የሚያጋልጥ  ተግባር እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል  ሰለሆነም  የዜጎች  የዲሞክራሲ መብቶችን በማፈን የሚድያ ነፃነት  ሊረጋገጥ አይችልምና።